Monday, July 22, 2013

ግብረሰዶማዊነት

ግብረሰዶማዊነት 
ለምን ?
የሰው ባህሪ በተፈጥሮ እና በአካባቢው ይቀረፃል :: በሕይወታችን የሚያጋጥሙን የተለያዩ ሁኔታዎችም ባህሪያችን በአካባቢያችን እንዲቀረስ ያደርጋሉ፡፡ ለምሳሌ የመጠጣት እና የመስከር ልምድ ያለው ሰው ለዚህ ባህሪው ምክንያት የሆኑ የቤተሰብ ወይም የአካባቢ ተፅዕኖዎች ይኖሩበታል::  ሆኖም ግን ይህ ሰው መጠጣት መፈለጉ ሳይሆን ጠጥቶ መስከሩ ኃጢያት ይሆንበታል:: እንዲሁም ሰዎች ግብረሰዶማዊ እንዲሆኑ የተለያዩ ምክንያቶች አስተዋጾ ያደርጋሉ::  እነዚህም ሰዎች ለተመሳሳይ ፆታ መሳባቸው ሳይሆን በፍላጎታቸው ምላሽ መስጠታቸው ግብረሰዶማዊ ይደርጋቸዋል::

ለግብረሰዶማዊነት ይህ ነው የሚባል መነሻ ባይኖርም የተለያዩ ሰዎች ወይም ምሁራን ለግብረሰዶማዊነት እንደመነሻ የተለያየ ምክንያቶችን ያስቀምጣሉ:: ግብረሰዶማዊነትም በተፈጥሮ በመወለድ የሚመጣ ነው ወይስ የምንማረው ባህሪ ነው የሚለው ብዙ ምሁራኖችን ሲያከራክር ቆይትዋል:: የግብረሰዶማዊነት መብት ተከራካሪዎችም ግብረሰዶማዊነት በተፈጥሮ የሚመጣ የማይለወጥ ባህሪ ነው ይላሉ:: ይሄም አመለካከት ያላቸው ሰዎች ’ኢሰንሻይሊስት’ ይባላሉ::  ባንፃሩ ደግሞ የስነልቦና ባለሙያዎች  ግብረሰዶማዊነት በግለሰብ ምርጫ የማይመጣ ይልቅስ የምንማረው ባህሪ እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡

ሰዎች በተለያየ ምክንያት ግብረሰዶማዊ ለመሆን ቢገፋፋሉም  ማንም ህፃን ግብረሰዶማዊ ሆኖ እንዳልተወለደ እና ግብረሰዶማዊነት በተፈጥሮ የሚመጣ እንዳልሆነ መፅሀፍ ቅዱስ ይነግረናል:: ይህ ማለት ግን ግብረሰዶማዊ ለመሆን ሁሉም ግብረሰዶማዊያን መርጥዋል ማለት አይደለም::

 መፅሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ሰውን ወንድ እና ሴት እድርጎ እንደፈጠረ ይናገራል (ዘፍ 1):: ትዳርም አንድ ወንድ እና አንዲት ሴት በቃል ኪዳን እና በፆታዊ ግንኙነት አንድ የሚሆኑበት ተቋም ነው (ማቴ 19: 4-6):: መፅሐፍ ቅዱስ ግብረሰዶማዊነትን ከተፈጥሮ ባህሪ ውጪ የሆነ  አሳፋሪ የእግዚሐብሔርን ሀሳብ የሚቃረን ኃጢያት እንደሆነ ይገልፃል (ዘሌ 18 :22 1 ዘዳ 23: 15 ሮሜ 1: 21- 31 ጢሞ 1: 10 ያቆ 1)  ከአዳም እና ሔዋን የኃጢአት ውድቀት በኋላ ሁሉም የሰው ዘር ከውድቀት ስር ነው:: ግብረሰዶማዊነትም የሰው ዘር በሙሉ ያለበት የሀጢያት ባህሪ አንዱ መገለጫ ነው:: ከአዳም ውድቀት በኋላ የአግዚአብሔር ፍፅም ፍጥረት ተመርዝዋል:: የሀጢአትም ዘር በስጋችን በመንፈሳችን በስሜታችን በአስተሳሰባችን ፀርስዋል::

አንዳንድ ግብረሰዶማዊያን እግዚአብሔር እንደዚህ አድርጎ እንደፈጠራቸው ያምናሉ ሆኖም ግን በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይህን ሀሳብ የሚደግፍ ቃል የለም:: አንድ ባህሪ በተፈጥሮ የመጣ ለማለት ከእግዚአብሔር የፍጥረት አላማ እና ስርዓት ጋር የተቆራኘ ሊሆን ይገባዋል እንጂ ከስጋዊ ፍላጎት እና ስሜት ጋር መገናኘቱ ተፈጥሮአዊ አያደርገውም:: “ሴቶቻቸውም እንኳ ለባህሪያቸው የሚገባውን ግንኙነት ባህሪያችው ላልሆነ ግንኙነት ለወጡ እንደዚሁም ወንዶች ለባህሪይቸው የሚገባውን ሴቶችን መገናኝት ትተው እርስ በእርሳቸው በፍትወት ተቃጠሉ ወንዶች ከወንዶች ጋር ነውር ፈፀሙ ለክፉ አድራጎታቸውም የሚገባቸውን ቅጣት በገዛ ራሳቸው ላይ አመጡ” ሮሜ 1፡27

 በአብዛኛው ኢትዮጲያውያን ግብረሰዶማዊነት የኢትዮጽያን ባህል ሀይማኖት እና ትውፊት የሚቃረን ተግባር እንደሆነ ይገልጻሉ:: በአብዛኛው ግብረሰዶማዊነት ከምዕራብያውያን ጋር በተያያዥነት ቢጠቀስም በኢትዮጲያ ውስጥ የተደረገ ጥናት  ያሳተፋቸው ግብረሰዶማዊያን በአብዛኛው የመጀመሪያ የወሲብ ልምምዳቸውን ከኢትዮጽያውያን ጎደኞቻቸው ዘመዶቻቸው እና አስተማሪዎቻቸው ጋር እንደሆነ ይገልፃል (Getnet Tadele (PhD) Under the Cloak of Secrecy: Sexuality and HIV/AIDS among Men who have sex with men (MSM) in Addis Ababa) ግብረሰዶማዊነት በማህበረሰቡ የሚነቀፍና ለመነጋገርም ከባድ የሆነ ርዕስ ነው:: ይህም በማህበረተሰቡ ውስጥ የኃጢአት ተግባር ከመባሉም ባሻገር በሀገሪቱ ሕገመንግስት ፔናል ኮድ 1957 አንቀፅ 600 በእስራት የሚያስቀጣ ሕገወጥ ተግባር ተደረጎ ተጠቅፆል:: በ1997 የታደሰውም የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ግብረሰዶሚያዊነትን ወንጀል አድርጎ ያስቀምጠዋል::

ጤናማ ያልሆነ አስተዳደግ ወይም ከቤተሰብ ጋር ያለ ግንኙነት ሌላው ለግብረሰዶማዊነት ተጠቃሽ መንስሄ ነው:: ለምሳሌ በአብዛኛው ለግብረሰዶማዊ ባህሪ ያላቸው ሰዎች ከተመሳሳይ ጾታ ካለው የቤተሰብ አባል ጋር መልካም ያልሆነ ግንኙነት ያላቸው እንደሆኑ ጥናቶች ያሳያሉ:: እንዲሁም በኢትዮጽያ ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት የተደረጉ ጥናቶች በልጅነት የሚደርስ ጾታዊ ጥቃት ለግብረሰዶማዊነት ሊያጋልጥ እንደሚችል ያሳያሉ::  ከላይ የተጠቀሰውም ጥናት ከ11 በልጅነታቸው ጥቃት ከደረሰባቸው ሰዎች 5ቱ ግብረሰዶማዊ እንደሆኑ ያሳያል::  ሰው ነፃ ፈቃድ ያለው ፍጥረት እንደመሆኑ በሕይወታችን ላይ ለሚያጋጥሙንን መልካም ሆነ መጥፎ አጋጣሚዎችን ተከትሎ የሚመጣ መልካም ሆነ ክፉ ተፅዕኖ የእኛ ምርጫ ትልቅ አስተዋፆ ያደርጋል::
እንዲሁም  ግብረሰዶማዊነት በተለያዪ ተጨማሪ ምክንያቶች ሊከሰት ይችላል፡፡ ልጆችም ለአቅመ አዳም /ሔዋን ሲደርሱ  (በአፍላነት እድሜ) ወንዶች ከወንዶች ጋር ሴቶች ከሴቶች ጋር አዳዲስ ነገሮች መሞከራቸው ያልተለመደ ነገር አይደለም::
ለተመሳሳይ ጾታ መሳብ የሚሰማቸውም ሰዎች ራሳቸውን  ከሌላው ሰው የተለዮ እንደሆኑ ከልጅነታቸው ማሰብ ይጀምራሉ:: ለግብረሰዶማዊነትም የሚያጋልጣቸው ባህሪም በልጅነታቸው ይታይባቸዋል:: ከአነዚህም ባህሪያት ለምሳሌ በተለምዶ ሴታሴትነት የምንለው ይኸውም በአይንና በእጅ መካከል ያለ ደካማ ቅንብር በእስፖርታዊ እንቅስቃሴ ላይ ደካማ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፤፡ ይህም ከጎደኞቻቸው እና በእኩኞቻቸው ዘንድ የሚያስከትለው ፌዝ አና ትችት የበለጠ ግብረሰዶሚያዊ እንደሆኑ እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል፡፡

ከግብረሰዶማዊነት ሕይወት መውጣት ይቻላል!
እንዴት?
1 ባህሪው ትክክል እንዳልሆነ ማመን
ግብረሰዶማዊ ሰዎች ባህሪውን በመለማመድ የሚያገኙትን የአጭር ጊዜ የደስታ እና የእርካታ ስሜት  ግብረሰዶማዊ ለመሆናቸው ምክንያት አድርገው ይወስዱታል:: ሆኖም ግን የማንኛውም ሰው ሰውነት በዚህ ባህሪ ውስጥ ላለ ተግባር የደስታ እና የእርካታ ምላሽ እንዲሰጥ ተደረጎ የተፈጠረ ነው:: ይህ ስሜት ግን የግብረሰዶማዊነት ማረጋገጫ አይደለም:: ስጋዊ ሰውነት ከሚሰጠው ምላሽ በአንፃሩ  በሕሊና የግራ መጋባት እና ኃፍረት እና የከፋ ፀፀት ሊሰማ ይችላል:: ይህም ስሜት ትክክል ላልሆነ ተግባር ትክክል የሆነ ምላሽ ነው::

2 ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት በማሳደግ
ከግብረሰዶማዊነት ሕይወት  ለመውጣት  መጀመሪያ ሙሉ ፈቃደኝነት ይጠይቃል፡፡ ከዚህም በኋላ ከልብ በሆነ ንስሃ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ያስፈልጋል፡፡ “ኃጢአታችንን ብንናዘዝ ከኃጢአታችን ሊያነፃን ከበደላችንም ይቅር ሊለን የታመነ ነው፡፡” 1 ዮሐ 1፡9 እንዲሁም በዘላቂነት ከእግዚአብሔር ጋር ቅርብ ግንኙነት ማዳበር እና በእርሱም ላይ በመታመን  አስፈላጊ ነው፡፡  ይህን ባህሪ ለማቆም ስጋን ማሽነፍ ትልቅ የሆነ ራስን መግዛት ይጠይቃል፡፡ ራሳችንን በመግዛት ሂደት ለእግዚአብሔር አርዳታ እራሳችንን አሳልፈን መስጠጥ አስፈላጊ ቢሆንም የራሳችንንም አስተዋፆ መዘንጋት የለብንም::  ለዚህ ባህሪ የሚያጋልጡ ለምሳሌ የሚድያ ውጤቶች፤ ፊልሞች እና ኢንተርኔት ከመጠቀም መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡

3 መጽሐፍ ቅዱስ ስለእኛ የሚለውን ማወቅ
በመጽሐፍ ቅዱስ ወደተጠቀሰችው የአንደኛው ክፍለዘመን ቤተክርስትያን ዞር ብለን ስንቃኝ ጳውሎስ “ አንዳዶቻችሁ በዚህ ዓይነት ሕይወት ነበራችሁ” 1ቆሮ 6 11 አያለ ግብረሰዶማዊ ለነበሩት ለቆሮንቶስ ቤተክርስትያን አባላት ሲናገር እናያለን:: በመቀጠልም “አሁን ግን በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስምና በአምላካችን መንፈስ ታጥባችዋል ተቀድሳችኋል ፀድቃችኋል” ይላችዋል::
ሰዎች የሀሰትን ገንዘብ ለመለየት የእውነተኛውን ገንዘብ ልዮ ባህሪያት እንደሚያጠኑት ሁሉ በግብረሰዶማዊነት ሕይወት ውስጥ ያሉ ሰዎችም አይምሮአቸውን በእግዚአብሔር ቃል በማደስ፤ እውነተኛ ማንነታቸውንም ለይቶ በማወቅ የእግዚሐብሔር ልጅነትን ሕይወት መለማመድ ይችላሉ፡፡

4 አመለካከትን መለወጥ
ከግብረሰዶማዊነት ሕይወት ለመላቀቅ በሚደረግ ጥረት ውስጥ ዋናው የጦርሜዳ አይምሮአችን ነው:: በአይምሮአችንም ውስጥ እንደቴፕ የሚያጠነጥነውን የሰይጣንን እና የሕሊናችንን የውሸት ድምጽ ለይተን ማወቅ ይኖርብናል:: እነዚህንም ውሸቶች በመለየት በእውነት መተካት አለብን:: ይህም ማለት “መቼም መለወጥ አልችልም” የሚለውን ሃሳብ “በክርስቶስ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ” (ፊሊ 4፡3) መተካት ማለት ነው::
5  ለውጥ ቀላል ሂደት እንዳልሆነ እንመን
ለውጥ ቀላል ሂደት አይደለም ምክንያቱም የሚለወጠው አንድን ባህሪ ብቻ ሳይሆን የህይወታችንን መስመሮች ሲቃኙ የነበሩ ብዙ ሃሳቦችን፤ ባህሪዎችን እንዲሁም ሰዎችን ነው:: በለውጥ ሂደት በመጀመሪያ ለመለወጥ ሙሉ ፈቃደኝነትን ይጠይቃል::  በመቀጠልም ስለራሳችን ያለንን የ “ይሄ ባህሪዬ ነው ማንነቴ ነው” የሚል አመለካከትን መለወጥ ያስፈልጋል::
በዚህ ሂደት ውስጥ ራሳችንን አናደርግም ብለን ከወሰነው ውሳኔ ማድረግ ተስኖን ብዙ የመውደቅና የመነሳት ሂደት ውስጥ ልናልፍ እንችላለን:: በምናልፍበት ሁኔታ ውስጥ ሁሉ ግን  ስሜታችንን ሀሳባችንን ሁሉ ለእግዚአብሔር በመንገር አብሮን እንዲሆን ክፍተት ልንሰጠው ይገባል::

በለውጥ ሂደት ውስጥ ብዙዎች ተስፋ በመቁረጥ ወደ ቀድሞ ሕይወታቸው ይመለሳሉ :: አንዳዶች ብዙ ይፀልያሉ አብዝተው መፅሀፍ ቅዱስ ያነባሉ:: የሚችሉትን ሁሉ በማድረግ ከአንዳንድ ባህሪዎች ራሳቸውን ለማላቀቅ ይሞክራሉ:: ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ ፀሎታቸው ትክክለኛ ያልሆነን አቅጣጫ የያዘ ነው  “ እግዚአብሔር ሆይ ለውጠኝ! ይህን ፍላጎት ከውስጤ አውጣ! ተቃራኒ ጾታ የሆነን ሰው መውደድ እንድጀምር እርዳኝ!” የመሳሰሉት ፀሎቶች ጥሩ ሆነው ሳለ በራሳቸው አመርቂ የሆነ ውጤት ማምጣጥ ግን አይችሉም:: ለምሳሌ  አረምን ወደአግዚአብሔር በመጮህ ወይም ደግሞ ላይ ላዮን በመቁረጥ ልናስወግደው አንችልም:: ይህን አረም ከስሩ ካልቆረጥነው መልሶ መላልሶ ያድጋል:: እንዲሁም የግብረሰዶማዊነት ሕይወት ዋና ምንጩ ተፈጥሮ ወይም ምርጫ ሳይሆን ባለፈው ህይወታችን ውስጥ ለአጋጥሙን ጉዳቶች ሕመማችንን  ለማከም ስንሞክር የምንሰጠው ትክክለኛ ያልሆነ ምላሽ ነው:: እውነተኛ ለውጥ የሚመጣው  ሙሉ በሙሉ ለእግዚሐብሔር በመገዛት እና በሕይወታችን የተጎዳንባቸውን ቦታዎች ለእርሱ እንዲፈውሳችው በመፍቀድ ነው:: ይህም ማለት ባለፈው ሕይወታችን ያሉ ሕመሞችን በመጋፈጥ ለእግዚአብሔር ፈውስ አሳልፎ መስጠት ነው::

6. መልካም ግንኙነቶችን ማዳበር
ግብረሰዶማዊነት መልካም ያልሆነ ግንኙነት ባለበት ቤተሰብ ወይም አካባቢ ከማደግ ሊከሰት አንደሚችል ሁሉ በመልካም ግንኙነት ሊፈወስ ይችላል::  በዚህም ምክንያት በዚህ ሕይወት ውስጥ ያሉ ሰዎች ጤናማ እና እግዚአብሔርን መፍራት ያለበትን ግንኙነት እንዲያዳብሩ በቤተክርስትያን መታቀፍ ጠቃሚ ነው:: ሆኖም ቤተክርስትያን መምጣት ብቻውን ለባህሪ ለውጥ ያለው አስተዋፆ በጣም አነስተኛ ሊሆን ስለሚችል በቤተክርስትያን ውስጥ ለሚገኝ ‘ሜንተር’ ሊሆን ለሚችል እና ለሚያምኑት ሰው ሙሉ በሙሉ ግልፅ የሚሆኑበትን ግንኙነት ማዳበር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

ማጠቃለያ

እንግዲህ በግብረሰዶማዊነት ሕይወት ውስጥ ላለ ከዚህም ሕይወት ለመውጣት ፍላጎት ላለው ሰው የዚህ ፁኅፍ ማጠቃለያው መልዕክት እንዲህ ነው፡፡


አንተ/ አንቺ በእግዚሐብሔር ሀምሳል፤ ለእግዚሐብሄር ክብር መገለጫ ውብ እና ድንቅ ሆነህ/ሽ የተፈጠርክ/ሽ ሰው ነህ/ሽ (ሮሜ 11፡36 መዝ 139:14) :: የሚያስፈልግህ/ሽ እግዚሐብሄር ብቻ ነው፤ እርሱ መልካም እና ጠቢብ (መዝ 145፡9) ፤ደግ እና ታጋሽ (2ጴጥ3፡9)  ፃድቅ እና ታማኝ (መዝ 33፡4) አዳኝ (ያቆ 1፤25) አምላክ ነው፡፡

ምናልባት ከአባት ወይንም ከአባትነት ቦታ ካለው ሰው ከደረሰብህ/ሽ ጥቃት የተነሳ የእግዚሐብሔርን አባትነት እና ፍቅር ለመቀበል ትቸገራለህ/ትቸገሪያለሽ:: ምናልባት ደግሞ ስርሄት የሌለው ሀጢያት አነደፈጸምክ/ሽ እና የገሀነምንም ዕጣ ማለፍ እንደማትችል/ይ ታስባለህ/ታስቢያለሽ::  ምናልባት ደግሞ በማንአለብኝነት ህይወትህን/ሽን የስጋዊ ፍላጎትህን/ሽን ለማርካት ብቻ ትኖራለህ/ትኖሪያለሽ፡፡

በማናቸውም ሁኔታ ውስጥ ብትሆን/ኝ እግዚሐብሄር  ግብረሰዶማዊ የሆነውን ሰው አይነቅፍም የግብረሰዶማዊነትን ባህሪ እና ድርጊት እንጂ (ዘሌ 18: 22-23 ሮሜ 1: 26- 27  1 ቆሮ 6: 9- 11)፡፡ እግዚሐብሔር  ከማይነጥፍ የእውነተኛ የአባትነት ፍቅሩ ሊያካፍልህ/ሽ እና ሕመምህን/ሽን ሊያክም ኃጢያትህን/ሽን ይቅር ሊል ሁሌ እጆቹን ወደ አንተ/አንቺ ዘርግቶ ይጠብቅሃል/ሻል:: እግዚሐብሔር አምላክህ/ሽ ብቻ ሳይሆን አባትህ/ሽ ጓደኛህ/ሽ አፍቃሪህ/ሽ መሆን ይፈልጋል፡፡ የምትፈልገው/ጊው ዘላቂ እና አውነተኛ ፍቅርን ከሆነ ከእግዚሐብሔር ውጭ ይህን ፍቅር መፈለግ ነፋስን እንደመከተል ነው፡፡ በእግዚሐብሔር ዘንድ ብቻ የደስታ የሰላም የፍቅር ሙላት አለና ወደ እርሱ ቅረብ/ቢ፤ ወደ እርሱ ሽሽ/ሺ፡፡
ምርጫው ያንተ/ ያንቺ ነው!

Recommended reading: http://www.desiringgod.org/blog/posts/same-sex-attraction-and-the-wait-for-change

17 comments:

  1. Fair enough! But, have you ever had a friend who is gay? Have you talked to anyone? I was just wondering coz you seem to have pretty straight forward ideas of how to get out of this. I personally don't think it's that easy. Would love to know your thoughts on this, if you please.

    ReplyDelete
    Replies
    1. Yes I guess and no, you know how it is in Ethiopia, that is why I preferred to blog about it instead. I used to work on a certain project that had a version of HIV/AIDS and Homosexuality, because of that I read a couple of researches and a true story book on a life of a homosexual in Ethiopia. Those readings changed my perspective completely on how it could be hard to be in this life let alone getting out of it. I totally don't want to give the impression that it is easy to get out. And if I gave that impression am really sorry! And all the steps I suggested are not easy at all!! These steps are on transformation of mind and building a relationship which are a difficult process that require so much time, discipline and dedication and God's help.

      Delete